የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት አስራ አንድ ክፍለ ከተሞች በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ነው። ብሩክ ሆስፒታል አካባቢ ዉሃ ልማት አጠገብ የሚገኘው የወረዳ 8 አስተዳደር በተለያዩ ማህበረሰቦች የሚታወቅ ከ20 በላይ ኤንባሲዎችን የቀፈ ደማቅ አካባቢ ነው። ትምህርት እና ገቢዎችን ጨምሮ አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶችን የሚሰጡ በርካታ ጽ/ቤቶችን ያካተተ ቁልፍ የመንግስት ተቋም ሆኖም እያገለገለ ይገኛል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ስትራቴጂካዊ አቀማመጥና አጠቃላይ አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ላይ ያለውን ጠቀሜታ አጉልቶ ያሳያል። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ለህብረተሰቡ ልማት ቁርጠኛ በመሆን ከተማዉ ብሎም ለክፍለ ከተማዉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆ አለው።
ራዕይ
አዲስ አበባን የአፍሪካ የብልጽግና ምልክት አድርጋ ማየት።
ተልእኮ
የውስጥና የውጭ ግንኙነትን በማጠናከር፣ የከተማዋን ገጽታ ግንባታ በማሳደግ፣ የተቋማትን አፈጻጸም በመከታተልና በውጤት ላይ በመገምገም የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የካቢኔ ውሳኔዎችን ተግባራዊ በማድረግ እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።
እሴቶች
ግልጽነት እና ተጠያቂነት ፤
ቅንነት ፣
ታማኝነት
ተነሳሽነት ፣
በጣም ጥሩ አገልግሎት ፣
የህግ የበላይነት ፣
በእውቀት እና በእምነት መምራት