በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የንግድ ጽ/ቤት የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ፡-
- በንግድ ድርጅቶች ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማካሄድ ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ማረጋገጥ
- የሚዛንና መስፈሪያ መሳሪያዎች ትክክለኛነት በማረጋገጥ ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት ማስፈን ፣
- በኢንስፔክሽን ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ነጋዴዎችን መለየት ፣
- በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው ከተገኙ የንግድ ድርጅቶች መካከል አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ፣፣
- በህገ-ወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው የተገኙ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊነት መመለስ፣
- የእሁድ ገበያዎችን ተደራሽነትን በማስፋትና ስታንዳርድ በማስጠበቅ በእሁድ ገበያዎች የምርት አቅርቦት መጠን ከ ማሳደግ፣፣
- መንግስት ድጎማ የሚያደርባቸውን ምርቶች በፍትሃዊነት ማቅረብ ፣
- የነጋዴ፣ የዘርፍ ማህበራትን በማጠናከር ሚናቸውን ማሳደግ
- የሸማች መብት ጥሰቶች እና የተከለከሉ ድርጊቶች ላይ ክትትል በማድረግ የሸማቹን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ
- በሸማቹ ህብረተሰብ፣ በነጋዴውና በባለድርሻ አካላት የሚቀርቡ ጥቆማዎችን በመቀበል ማጣራትና መፍታት ፣
- ከሸማቾች ጋር በተያያዘ የተደራጁ እና ለሚደራጁ የሲቪክ ማህበራት በማጠናከር ሚናቸዉን ማሳደግ፣