በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የሴቶችና ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ፡-

  1. ለሴቶች የማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ መስጠት
  2. ከፍለው መማር ለማይችሉ ሴቶች የትምህር እድልና ድጋፍ ማመቻቸት
  3. ሴቶችን በገቢ ማስገኛ ዘርፎች እንዲሰማሩ ድጋፍ መስጠት
  4. ሴቶች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ማመቻት
  5. ሴቶች የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ማመቻት
  6. ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት
  7. ለጥቃት ተጎጂዎች ተግባራዊ ምላሽ መስጠት : የህግ ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ
  8. አማራጪ የህፃናት እንክብካቤ (ጉድፍቻ ,አደራ ቤተሰብ ) አገልግሎት መስጠት
  9. ምክር ምክክርና አመራር አገልግሎት መስጠት
  10. ለህፃናት የስነ ልቦና አገልግሎት መስጠት
  11. ለህፃናት ቤተሰብ ምክር አገልግሎት መስጠት
  12. የአልሚ ምግቦችን ለእርጉዝ እናቶችና ጨቅላ ህፃናት አቅርቦት ክትትል
  13. ተጠቃሚዎችን ከመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ማተሳሰር
  14. ለተጠቃሚዎች የኑሮ ማሻሻያ አገልግሎት መስጠት
  15. ለከፋ የማህበራዊ ችግር ውስጥ ለገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ
  16. ለእድሮች የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መስጠት
  17. ለአካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን የተሃድሶ አገልግሎት መስጠት
  18. የሰው ሰራሽ አካልና አካል ድጋፍ አገልግሎት ማመቻት
  19. አቅም ለሌላቸው አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን በነፃ ህክምና/የጤና መድህን አገልግሎት ማመቻቸት