Welcome to Lideta Subcity Woreda 8 Administration!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር በሰላም መጡ!       Baga Gara Kutaa Magaalaa Lideta Aanaa 8 Nagaan Dhuftan!

ቁጥራዊ መረጃ

16,000

በወረዳዉ የሚኖር የህዝብ ብዛት

2211

የወረዳዉ ስፋት m2

2441

የወረዳዉ ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ

የዋና ስራ አስፈፃሚዉ መልእክት

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የአገልግለት ዕለትን ለተገልጋይ ብቻ በማዋል የህዝብ እሮሮን ለመቀነስ ብሎም በተገልጋዮች የሚነሱ አንገብጋቢ የሆኑ ጥያቄዎችን በአግባቡ አድምጦ ለመመለስ በሁሉም ጽህፈት ቤቶች አገልግሎትን በአንድ ማዕከል መስጠት ከጀመረ ጊዜያትን አስቆጥሯል ፡፡

በተለይም በተለያዩ ምክንያቶች ለአሳዛኝ ችግሮች የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በርህራሄ እና በአክብሮት እያዳመጠ ህግና መመሪያ በሚፈቅደው መንገድ ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠትና በመፍታት፤ችግሮችና ቅሬታዎች ወደተነሱበት ተቋማት በቀጥታ ስልክ በመደወልም ጭምር በግልፅ በማነጋገር እልባት እየሰጠ ይገኛል። ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላልና ተገልጋዮቻችን ወደ እኛ ኑ ጥያቄያችሁን አቅርቡ። በእኛ ደረጃ የምንፈታውን ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን ። ከኛ በላይ የሆነውን ለሚመለከተው አካል እናስተላልፋለን። የማንፈታውን ከእናንተ ጋር እንግባባለን። ይህ የ2018 የአገልግሎት አሰጣጥ መርሀችን ነው። .... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ደረጄ ፈይሳ , የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ
image description

የወረዳዉ አመራሮች

ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ምቹ፣ ማራኪ እንዲሁም ውብና ጽዱ የመኖሪያ መንደር ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

የህብረተሰቡን አኗኗር ዘይቤ እየቀየሩ፤ እያዘመኑ የሚገኙ የተቀናጀ ሞዴል የብሎክ ስራ በልደታ ክ/ከተማ ውስጥ ብሎኮችን የማዘመን ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡን በማስተባበር ‎ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ፅዱ፣ ምቹና ውብ እንዲሁም ማራኪ አካባቢን መፍጠር ያስፈልጋል በማለት አስተዳደርሩ ሰንቆ በተነስው ተግባር በሁሉም ወረዳዎች እና ብሎኮች ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። "በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ" እቅድ አንዱ ግብ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ መፍጠር ሲሆን ምቹና ውብ እንዲሁም ማራኪ አካባቢ እንዲፈጠር ከነዋሪው ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ይገኛል። በተፈጠረው የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ የክ/ከተማው ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለኑሮ ምቹና ተስማሚ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ ብሎኮቹን በማልማት፣ በማፅዳት፣ በማስዋብ የተለያዩ ተግባራት እያከናወኑ ይገኛል፡፡ አስተዳደሩ ሞዴል ብሎኮችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሌሎች ተጨማሪ ምቹ ብሎኮችን በመፍጠር አካባቢያቸውን ምቹ፣ ውብና ጽዱ እና ማራኪ መኖሪያ መንደር ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። እየተከናወኑ ከሚገኙት የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ተግባራት መካከል በጽዳት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በከተማ ግብርና፣ በሰላምና ፀጥታ፣ ECD፣ በውስጥ ለውስጥ መብራት፣ የመሳሰሉት ስራዎች ተካተውበታል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ምክር ቤት አባላት በወረዳው በኢንሼቲፍ የተሰሩ ስራዎችን የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ አስጎብኝተዋል።

አቶ ደረጄ እነዚህ ስራዎች በባለሀብቶች እና በነዋሪዎች በጎ ፈቃደኝነትና ትብብር የተሰሩ ናቸው። የተጠናቀቁት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል በግንባታ ላይ ያሉት ደግሞ በቅርቡ ተጠናቀው ወደ ስራ ይገባሉ በማለት ተናግረዋል። በጉብኝቱም በጣም መደሰታቸውንና እንደዚህ አይነት ስራዎች አዲስ አበባን ለማስዋብ እየተሰራ ያለውን ስራ በእጅጉ የሚደግፍ ነው ሲሉ የምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
''በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ!!'' በሚል መሪ ቃል የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አቅጣጫዎች ያለበት ደረጃ የወረዳው ጠቅላላ አመራሮች በተገኙበት በስፋት ተገመገመ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ''በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ !!'' በሚል መሪ ቃል የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አቅጣጫዎች ያለበት ደረጃ የወረዳው ጠቅላላ አመራሮች በተገኙበት በስፋትና በጥልቀት ተገምግሟል። በግምገማ መድረኩ በዋነኝነት:- የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራዎችን፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች፣ ከሰው ተኮር ተግባራት፣ የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ ከመፍጠር፣ ከሪፎርም ስራ አኳያ የተሰሩ ተግባራት አፈፃፀም ፣ በሪፓርት በዝርዝር ቀርቦ በስፋት ተገምገሟል። በመጨረሻም የተያዙት ዕቅዶች ልዩ ትኩረት የሚፈልጉ በመሆናቸው በውጤት ለማጠናቀቅ ሁሉም አመራር በቁርጠኝነትና በጊዜ የለኝም መንፈስ ሊረባረብ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል። ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ህዝባዊ የዉይይት መድረክ ተካሔደ።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር "የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል የሕዝባዊ የውይይት መድረክ በዛሬዉ እለት ተካሔዷል። በወረዳዉ በተካሔደው የውይይት መድረክ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ባለሀብቶችና ምሁራንን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል። የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ቱሩፋት በሚል ርዕስ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሕዝብ መድረኮች ላይ ከነዋሪዎቻችን ለተነሱ ጥያቄዎች፣ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች በተግባር የተሰጡ ምላሾች፣ እንዲሁም ቀሪ ሥራዎችን አስመልክቶ በወረዳዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ደረጄ ፈይሳ በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በተካሔደው የህዝብ የውይይት መድረክ አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ የአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ፣ወ/ሮ ተስፋነሽ ጋሻው የክፍለ ከተማው ንግድ ፅ/ቤት ሀላፊና የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ በጋራ መርተውታል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማችን በተለያዩ የልማት ሥራዎች አስደናቂ ስኬቶች የተመዘገቡት መንግሥትና ሕዝብ አንድ ሆነው በመቀናጀትና በመናበብ ሊፈጽሟቸው በመቻላቸው መሆኑን በውይይቱ ተብራርቷል። በውይይቱ በመንግሥትና በሕዝብ ትብብር የተሰሩ በርካታ ሥራዎችን እና የተመዘገቡ ውጤቶችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ እንዲሁም የሕዝብን ተሳትፎ ይበልጥ በሚያረጋግጡ ቀጣይ የጋራ ዕቅዶች ላይ ዳር ማድረስ እንደሚደሚባ መግባባት ተፈጥሯል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
የመደመር መንግሥት እይታን ፣የዘርፎች እመርታ በማብዛት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን!!!

‎ ‎በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል የሚሰጠው አራተኛ ዙር የብልጽግና ታችኛው አመራር እና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ተጠናክሮ ቀጥላል ። ‎ ‎በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስብሃት መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት "በመደመር እይታ የግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን" ፥ "የቱሪዝም" ፥ "የአምራች ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት እመርታ" በሚሉ አራት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የአመራራችንና የአባላችን የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለማረጋገጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል።አራተኛው ዙር የብልጽግና ታችኛው አመራር እና አባላት የአቅም ግንባታ የስልጠና ሰነድ በማቅረብ የስልጠና ዓላማ አባሉ በየደረጃው የሚገኝ ታችኛው አመራር እና አባላት መንግሥት ለነዚህ ዘርፎች የሰጠውን ትኩረት በመረዳት የብልጽግና እሴት እና የመደመር መንግሥት የአባልነት ባህሪን በመላበስ የተጀመረውን ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ በውጤታማነት በመደገፍ የሚያስችል አቅም ነው። በመድረኩ በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል የሚሰጠው ስልጠናው ዋና አላማ በፓርቲያችን እሳቤዎች ፣ በመንግስት ፖሊሲዎች የጋራ እሳቤ በመያዝ ሁለገብ ግንባር ቀደም የሆኑ አመራር እና አባል ለመፍጠር ለሚደረገው ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር እና ቀጣይ በስኬቶቻችን ተሸላሚ ለመሆን የአመራሩንና የአባሉ የአስተሳሰብ አንድነት እንደሚገነባ እና ለበለጠ ተልዕኮ ስኬት እምርታ ማረጋገጥ ተክቶ በመስራት ለቸግባር ስኬታማነት ማረጋገጥ ስልጠናው አይነተኛ ሚና እንዳለው መድረኩን የመሩት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስብሃት ገልፀዋል። ‎ በማጠቃለያም የስልጠና ተሳታፊዎች የስልጠና ዓላማ አባሉ በየደረጃው የሚገኝ ታችኛው አመራር እና አባላት መንግሥት ለነዚህ ዘርፎች የሰጠውን ትኩረት በመረዳት የብልጽግና እሴት እና የመደመር መንግሥት የአባልነት ባህሪን በመላበስ የተጀመረውን ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ በውጤታማነት በመደገፍ የሚያስችል አቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን አስፈላጊ እንደሆነም ገልጿል።

image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 አስተዳደር በኢቶ ኮደርስ አርቴፊሻል ኢንተለጀስንስ ትግበራ ዙሪያ ለስራ ሂደቶች ግንዛቤ ሰጠ።

በዕለቱም ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ፈይስ ዘመኑ የቴክኖሎጂ ስለሆነ በኢቶ ኮደርስ እራሳችሁን በማበልፀግ ስራዎችን በአጭር ጊዜ በመስራት እና ቀልጣፍ አገልግሎትን በመስጠት የማህበረሰቡን እርካታ በማሳደግ ዉጤታማ መሆን ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል ። የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ስበአት እንደገለጹት የኢቶ ኮደርስ ተግባር በአገራችን ለውጥ የሚያመጣ ስለሆነ ሁሉም የወረዳችን ሰራተኞች ቶሎ ወደ ተግባር መግባት አለባቸው ብሏል።

image
image
image

አቅጣጫ ጠቋሚ

በወረዳዉ ህንፃ ዉስጥ ያሉ ፅህፈት ቤቶች አቅጣጫ ጠቋሚ

ግራውንድ ፍሎር የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት

አንደኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ንግድ ጽ/ቤት

ገቢዎች ጽ/ቤት

ሁለተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ስራና ክህሎት ጽ/ቤት

ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት

የህፃናት ማቆያ ዴይኬር

ሶስተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ፐብሊክ ሰርቪና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት

ፓርቲ ጽ/ቤት

አራተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት

ምክር ቤት

ከተማ ግብርና ጽ/ቤት

ትምህርት ጽ/ቤት

አምስተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

ህብረት ስራ ጽ/ቤት

ወጣትና ስፓርት ጽ/ቤት

ስድስተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ፋይናንስጽ/ቤት

ፅዳትና ከተማ ውበት ጽ/ቤት

ቤተመጽሀፍት

ሰባተኛ ፎቅ የሚገኙ ጽ/ቤቶች

ዋና ስራ አስፈፃሚ

ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት