image
image
image
image
image

የመደመር መንግሥት እይታን ፣የዘርፎች እመርታ በማብዛት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን!!!

ህዳር 29, 2017
‎ ‎በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል የሚሰጠው አራተኛ ዙር የብልጽግና ታችኛው አመራር እና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ተጠናክሮ ቀጥላል ። ‎ ‎በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስብሃት መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት "በመደመር እይታ የግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን" ፥ "የቱሪዝም" ፥ "የአምራች ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት እመርታ" በሚሉ አራት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የአመራራችንና የአባላችን የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለማረጋገጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል።አራተኛው ዙር የብልጽግና ታችኛው አመራር እና አባላት የአቅም ግንባታ የስልጠና ሰነድ በማቅረብ የስልጠና ዓላማ አባሉ በየደረጃው የሚገኝ ታችኛው አመራር እና አባላት መንግሥት ለነዚህ ዘርፎች የሰጠውን ትኩረት በመረዳት የብልጽግና እሴት እና የመደመር መንግሥት የአባልነት ባህሪን በመላበስ የተጀመረውን ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ በውጤታማነት በመደገፍ የሚያስችል አቅም ነው። በመድረኩ በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ቃል የሚሰጠው ስልጠናው ዋና አላማ በፓርቲያችን እሳቤዎች ፣ በመንግስት ፖሊሲዎች የጋራ እሳቤ በመያዝ ሁለገብ ግንባር ቀደም የሆኑ አመራር እና አባል ለመፍጠር ለሚደረገው ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር እና ቀጣይ በስኬቶቻችን ተሸላሚ ለመሆን የአመራሩንና የአባሉ የአስተሳሰብ አንድነት እንደሚገነባ እና ለበለጠ ተልዕኮ ስኬት እምርታ ማረጋገጥ ተክቶ በመስራት ለቸግባር ስኬታማነት ማረጋገጥ ስልጠናው አይነተኛ ሚና እንዳለው መድረኩን የመሩት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስብሃት ገልፀዋል። ‎ በማጠቃለያም የስልጠና ተሳታፊዎች የስልጠና ዓላማ አባሉ በየደረጃው የሚገኝ ታችኛው አመራር እና አባላት መንግሥት ለነዚህ ዘርፎች የሰጠውን ትኩረት በመረዳት የብልጽግና እሴት እና የመደመር መንግሥት የአባልነት ባህሪን በመላበስ የተጀመረውን ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ በውጤታማነት በመደገፍ የሚያስችል አቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን አስፈላጊ እንደሆነም ገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች