image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የብሎክ ካውንስል ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡

ጥቅምት 29, 2017
በጉባኤው ላይ የብሎክ ካውንስል ተጠሪዎች ሰራተኞችና አመራሮች ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ፈይሳ እንደተናገሩት አስተዳደሩ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ አውስተው፣ ከአስተዳደሩ ጥረት ጎን ለጎን ሕብረተረሰቡ በአካባቢው በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ልማትን ከማፋጠን ባሻገር በመንግሥትና በሕብረተሰቡ መካከል ያለውን በጋራ የመሥራት ባሕል እንደሚያጠናክር አመላክተዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ሰለሞን በበኩላቸው የሕብረተሰቡን የልማት ፍላጎት የማሟላት ሥራ በመንግሥት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን በህዝቡ ተሳትፎ ሊታገዝ እንደሚገባው ገልጸው በሕብረተሰብ ተሳትፎ በተከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ የብሎክ ካውንስል አደረጃጀቶች በሀብት ማሰባሰብ፣ በግንባታ ሥራዎች አፈጻጸም፣ በአካባቢ ጽዳት፣ በሰላምና ጸጥታ ስራዎችና በሌሎች ተግባራት ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸው፣ አሁንም የሕብረተሰብ ተሳትፎ ሥራዎችን በማጠናከር ክፍተቶችን በማስተካከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የጉባኤው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በተያዘው በጀት ዓመት በሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም ተሳትፏቸውን በማሳደግ በርካታ የልማት ስራዎችን ከመንግሥት ጋር በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች