image
image
image
image
image

ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩ የልማት ስራዎች ለአገልግሎት ክፍት አደረገ።

ግንቦት 2, 2017
የወጣቶችና የህፃናትን የስፖርት ተሳትፎን ለማሳደግ በማለም ያስገነባውን የእግር ኳስ ሜዳ ፕሌግራውንድ፣ የአስፓልት መንገድ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል። ስነ-ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቢሮ ሀላፊ፣ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴና አመራሮች፣ የወረዳ ኃላፊዎች፣ ወጣቶች፣ ነዋሪዎች እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በተገኙበት ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል። የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደገለፁት ሜዳው ፕሌ ግራውድ የወጣቶች ህፃናት ጊዜያቸውን በአዎንታዊ ተግባራት እንዲያሳልፉ እና የስፖርት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል። የተሰሩ የልማት ስራዎች ለአካባቢው ወጣቶች ነዋሪዎች ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ መሰል ልማቶች በቀጣይነት እንደሚስፋፉ ገልፀዋል ። በቀጣይም የህዝቡን ተሳትፎ በማዳበር የማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን ከዚህ በበለጠ በመስራት የወጣቶችን የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን በማለት ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች