image
image
image
image
image

ከተረጂነት በመላቀቅ እራስንና ሀገርን ማበልፀግ እንደሚገባ ተገለፀ ።

የካቲት 7, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 የከተማ ግብርና ጽ/ቤት በኑሮ ዝቅተኛ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች የእንቁላል ጣይ ዶሮ፣የመኖ እና የኬጅ ስርጭት አደረገ። በዕለቱ ተገኝተዉ የንግግር መክፈቻ ያደረጉት የወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ፈይሳ የሌማት ትሩፋት ተግባርን መንግስት በትኩረት እየሰራበት ያለ ሲሆን ዛሬ የምንሰጣቹሁን መነሻ በማድረግ ከእራስና ከቤተሰቡ አልፎ ለገበያ በማዋል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት መዉጣት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የባለ ብዙ ፀጋዎች ባለሀብት በመሆኗ በሌማት ትሩፋት ተግባራት ላይ ሁሉም ማህበረሰብ በትጋት በመስራት ከተረጂነትና ከልመና በመዉጣት እራሱንና ሀገሩን ማበልፀግ እንዳለበት ተናግረዉ ለቀጣይ ለሚካሄደው 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን ለወረዳዉ ነዋሪዎች ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የወረዳ 08 የከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላቸዉ አበራ በበኩላቸው ይህ ተግባር በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራ ይገኛል ምርትና ምርታማናትን ለማሳደግ በተለያዩ ተግባራት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ያለዉን የኑሮ ዉድነት ለመቀነስ ጽ/ቤቱ በትኩረት መስራቱን ገልፀዋል ። አቶ በላቸዉ አክለዉም የሚሰጧችሁን ዶሮዎች የሚሰጣቹሁን ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ በመቀበል የዶሮዎች ጤና በመጠበቅ ከራሳችሁ አልፋቹህ ለገበያ በማዋል ተጠቃሚነታቸዉን ማረጋገጥ እንዳለባቸዉ መልዕክት አስተላልፈዋል ። የካቲት 10/6/2018 ዓ.ም

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች