image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ስነ-ምግባርና ፀረ -ሙስና ቡድን" ትዉልድን በስነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል ከወጣቶች ጋር የፓናል ዉይይት አካሂዷል ።

ህዳር 12, 2017
በአለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ በሀገራችን ለ21 ጊዜ የሚከበረዉን የፀረ -ሙስና ቀንን አስመልክቶ ከወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከወጣቶች ጋር የፓናል ዉይይት ተካሄደ። በትዉልድ ግንባታ ላይ እና በተቋማት አሰራር ላይ በትኩረት በመስራት ሙስናን መከላከልና ጥቆማ በመስጠት ሙስናን ማጋለጥ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን በዉይይቱ ላይ ተገልጿል ። በተቋማት ዉስጥ ብልሹ አሰራርን በማጋለጥ ፣የአሰራር ግልፀኝነትን በማስፈንና የወጣቶችን ስራ አጥነት በመቀነስ የዜጎችን የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ቡድን ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ያሳብ ተናግረዋል ። የወረዳ 08 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በዕምነት ሙስና ለሀገራችን ነቀርሳ የሆነና በማንኛውም ደረጃ ያለዉን ማህበረሰብ የሚጎዳ በመሆኑ ወጣቶች የሙስናን አስከፊነት በመረዳት ጥቆማ በመስጠት ሙስናን መዋጋት አለባችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች