image
image
image
image
image

"ሀገር በቀል እሴቶች ለዘላቂ ሰላም" – ልደታ ወረዳ 08 እና 06 ከወጣቶች ጋር ተወያየ።

ጥቅምት 27, 2017
ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 እና 06 ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ ወጣቶችን ያሳተፈ "ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል ለትውልድ እሴቶች ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ዙሪያ ሰፊ የውይይት መድረክ ማካሄዱን አስታውቋል። ውይይቱ የተካሄደው ከወረዳው ከተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ከሚወክሉ ወጣቶች ጋር ሲሆን፣ የሰላም ባህልን በወጣቱ ዘንድ ለመገንባት አላማ ያነገበ ነው። ውይይቱን የመሩት የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ አበራ እንደተናገሩት፣ ወጣቶች የሀገር ግንባታ ምሰሶ ከመሆናቸው ባሻገር፣ በማኅበረሰብ ውስጥ ሰላምን እና መቻቻልን በማስፈን ረገድ ወሳኝ ሚና አላቸው። አቶ ሄኖክ አክለውም፣ "ሰላም ከውጭ የሚመጣ ሳይሆን በውስጣችን የምንገነባው እሴት ነው። ይህንን ሀገር በቀል የሰላም እና የመቻቻል እሴት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በቅድሚያ እኛ ራሳችን የሰላም አምባሳደር መሆን አለብን። ወረዳው የፀረ-ሰላም ኃይሎችን ተጽዕኖ ለመከላከል የወጣቱን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው" ብለዋል። የልደታ ወረዳ 08 የሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አፈወርቅ ቦጋለ በበኩላቸው፣ የሰላም ማስፈን ሥራ የፖሊስና የጸጥታ አካላት ብቻ ሳይሆን የመላው ኅብረተሰብ በተለይም የንቁ ወጣቶች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል። አቶ አፈወርቅ እንዳሉት፣ "መቻቻልና ሰላም ሲኖር፣ የሕግ ማስከበር ሥራው ይቀላል። ፖሊስ ወንጀልን ከመከሰቱ በፊት፣ ወጣቶች አለመግባባቶችን በውይይት እንዲፈቱ የማድረግ የሰላም ባህልን ሲያዳብሩ፣ የኅብረተሰብ ደኅንነት ይረጋገጣል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚኒቲ ክፍል ከወጣቶች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሰላምን ተቋማዊነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው" በማለት አፅንዖት ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ ወጣቶቹ ሀሳባቸውን በግልጽ በማንሳት፣ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች